The Annual Rent Guideline Increase for 2025 is 2.5%
Tenant Hotline: 416-921-9494

Above Guideline Rent Increases - (አማርኛ) Amharic

ከመመሪያ በላይ የሚደረግ የኪራይ ጭማሪ

ማሰታወሻ:- የሚከተለው መረጃ የሚገናኘው በተለይ ለትርፍ ለሚከራዩ (ከግለሰብ፣ ወይም ከንግድ ተቋማት) እና ኦንታሪዮ ውሰጥ ላሉ ቤቶች ሲሆን አፓርትመንት፣ ቤት፣ ክፍል፣ ቤዘመንት፣ ኮንዶ አፓርትመንት ወዘተ የሚያጠቃልል ነው።

የማሀበረሰብ ቤቶች (ቲ.ሲ.ኤች.ሲ) ለተርፍ ያለተቋቋሙ ቤቶች፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ የተማሪዎች ማደሪያ፣ መጠለያ፣ እሰር ቤት፣ የእንክብካቤ ቤቶች፣ ከቤቱ ባለቤት ሳይሆን ከተከራይ የሚከራዩ፣ ወይም ከቤቱ ባለቤት ገር ኩሸና እና መታጠቢያ ቤት የሚጋሩ ከሆነ ሀጎቹ የተለዩ ይሆናሉ።

አንዳንዴ በሚኖሩበት ቤት ሁኔታ ምክንያት ሂደቱ/አካሄዱ ሊመሳሰል ወይም በፍፁም ሊለያይ ይችላል። ከእንደዚህ ዓይነት ቤቶች ጋር የሚገናኙ ጥያቄዎች ካልዎት ወደ ተከራዮች የጥሪ ማእከል ይደውሉ ወይም ለበለጠ መረጃ ድረ ገፃችንን ይመልከቱ።

ከግሽበት መመሪያ የኪራይ ጭማሪ በተጨማሪ የኦንታሪዮ ህግ የቤት አከራዮችከመመሪያው በላይ የሆነ የኪራይ ጭማሪወይም በአጭሩ አይ ጭማሪ እንዲያመለክቱ ይፈቅድላቸዋል።

የቤት አከራዮች በተለያዩ ምክንያቶች ኪራይ ለመጨመር ሊያመለከቱ ይቸላሉ እነዚህም:

  • የተከፈለበት እና ያለቀ ትልቅ ሥራ ለምሳሌ (በበረንዳዎቸ፣ በአሳነሰሮች/ሊፍቶች)
  •  ወጪ ቀናሽ ለሆኑ (ዝቅተኛ ሀይል እና ፍሳሽ ያላቸው መብራቶች እና ሽንት ቤቶቸ) ሥራ የተከፈለ እና ሰራው ያለቀ ከሆነ
  • ለደህንነት ጥበቃ ሥራ (ለደህንነት ካሜራዎች) የተከፈለ እና ሰራው ያለቀ ከሆነ
  •  ተደራሽነት ላላቸው (የተሽከርካሪ/ዊልቼር መወጣጫዎች፣ አውቶማቲክ የበር መክፈቻዎች) ሥራ የተከፈለ እና ሰራው ያለቀ ከሆነ
  • በአከራዩ ላይ በጣም የተጋነነ የንብረት ግብር የተጠጣለበት ከሆነ

1 እሰከ 4 ለተዘረዘሩት የኪራይ ጭማሪ ምክንያቶች አከራይ 9 በመቶ የኪራይ ጭማሪ በአንድ በማመልከቻ ሊጠይቅ ቢችልም፣ የአከራይ እና የተከራይ ቦረድ (ኤል.ቲ.ቢ) አከራዩ ይህንን ጨማሪ ለሶስት አመታት እንዲያከፋፍል ሊያሰገድደው ይችላል። በዚህም መሠረት አከራዩ በአንድ ዓመት ሊያገኝ የሚቸለው ጭማሪ 3 በመቶ ይሆናል።

ለምሳሌ፣ አከራዩ 9 በመቶ ጭማሪ 2022 . ቢያገኝ፣ ኪራዩን 4.2 በመቶ ይጨምራል (1.2 በመቶ 2022 . የመመሪያ ጭማሪ ሲደመር 3 በመቶ) 5.5 በመቶ 2023 . ይጨምራል ( 2.5 በመቶ 2023 የመመሪያው ጭማሪ ሲደመር 3 በመቶ) 5.5 በመቶ 2024 . ይጨምራል ( 2.5 በመቶ 2024 የመመሪያው ጭማሪ ሲደመር 3 በመቶ) ይሆናል ማለት ነው።

በጣም ለተጋነነ የንብረት ግብር ማመልከቻ የሚሰጥ አማካኝ የሆነ የኪራይ ጭማሪ ባይኖርም፣ አብዛኛዎቹ

ማመልከቻዎች የኪራዩን መጠን 0.5 እሰከ 1.0 በመቶ እንዲጨመር በፅሁፍ ይጠይቃል።

አከራዩ መቼ እንደሚጠይቅ/ተከራዩስ መቼ መክፈል እንዳለበት

አከራዩ ከመመሪያው በላይ የኪራይ ጭማሪ ለማድረግ ከአከራይ እና ተከራይ ቦረድ ፈቃድ ማግኘት አለበት፣ ከቦረዱ ፈቃድ ሳያገኝ ከመመሪያው በላይ የኪራይ ጭማሪ ተከራዩ እንዲከፍል ማሰገደድ አይችልም።

ህጉ በዚህ የኪራይ ጭማሪ ጉዳይ አሰገራሚ ነገር አለው። ይኸውም ማመልከቻው ከቀረበ እና ክርከሩ እሰኪሰማ ደረስ በወራቶች የሚቆጠር ከፈትተ እያለ አከራዩ ማመልከቻውን ለቦርዱ ካሰገባ በኋላ እና ወሳኔ ከመሰጠቱ በፊት ገንዘቡ እነዲከፈለው መጠየቅ መቻሉ ነው።

በተጨማሪም አከራዩ ኪራይ ለመጨመር ጠይቆ ገና ውሳኔ ያለተሰጠ ከሆነ ተከራዩ ከተጠየቀው ጭማሪ ውሰጥ ከመመሪያ በላይ የተጠየቀውን ትቶ የመመሪያውን ጭማሪ ብቻ ሊከፍል ይችላል።

ከመመሪያ በላይ የተጠየቀውን ጭማሪ ከወሳኔው በፊት አለመክፈል ሊያሰከትል የሚችለው ብቸኛ ችግር ቦረዱ የተጠየቀውን ከመመሪያ በላይ ኪራይ ጭማሪ ወደኋላ ሄዶ እንዲከፈል ከወሰነ ነው።

አንዳንድ ተከራዮች ከመመሪያ በላይ የተጠየቀውን ጭማሪ ከውሳኔ በፊት ከፈለው ከውሳኔ በኋላ ተመላሽ ገንዘብ የሚያገኙ ከሆነ መጠበቅን ይመረጣሉ። ሌሎች ደግሞ አከራዩ በህግ ጭማሪውን እሰከሚያገኝ ድረሰ አንድ ሳንቲም ለአከራዪ ለመሰጠት አይፈልጉም። ለማንኛውም ጭማሪውን የመክፈልም ሆነ ያለመክፈል ምርጫ የተከራዮ ነው።

ከመመሪያ በላይ ጭማሪን መከራከር

ተከራዩች ከመመረያ በላይ ጭማሪን ለመከራከር ከሚያሰችሏቸው በዙ አማራጮች ወሰጥ፣

  • ምንም አለማድረግ
  • ጭማሪውን እራስን ወክሎ ለመከራከር መደራጀት
  • ከጎረቤቶች ጋር መቀናጀት
  • ኤፍ ኤም ከማዳረስ እና ከማደራጀት ቡድን ጋር አብሮ መስራት

የቶሮነቶ ከተማ የኤፍ.ኤም.ቲ.ኤ የማዳረስ እና የማደራጀት ቡድንን በገንዘብ በመርዳት ተከራዮች ከመመሪያ በላይ የኪራይ ጭማሪውን እንዲከላከሉ እና እነዲከራከሩ በማድረግ ኪራይን ተመጣጣኝ ያደርጋል። እኛ በየአመቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ኪራይ ለቶሮንቶ ለተከራዮች እናድናለን። የማዳረስ እና የማደራጀት ቡድኑ ምን አይነት አማራጮች እንዳልዎት ያሳወቆታል በተጨማሪም ትክክለኛ የህግ ምክር ሊያገኙ ወደሚችሉበት የህግ አገልግሎት በመላክ ለገዳዩ እርዳታ እነዲያገኙ ያደርጋል።

በተከራይ አከራይ ቦርድ ገና ውሳኔ ያላገኘ ከመመሪያ በላየ የኪራይ ጨማሪ ማሰታወቂያ ከደረሰዎት የማዳረሰ እና የማደራጀት ቡድኑ ያግዞታል። በ416 413 9442 ወደ ቡድኑ ዛሬውኑ በመደወል ከመመረያ በላይ ጭማሪውን ለመከላከል ያልዎት አማራጭ ምን እነደሆነ ይጠየቁ በተጨማሪም በሚኖሩበት ህንፃ ውሰጥ በአማራጮቹ ላይ ውይይት ለማድረግ ፍላጎት ካልዎት ይጠይቁን።

ሰለየማዳረስ እና የማደራጀት ቡድኑ የበለጠ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ።

March 27, 2025